መፍትሔ ያጣ ትውልድ
ተጳፈ
በዳንኤል አላዩ ዘለቀ
octo 11 2014
እነሆ አለም ከተፈተረች ብዙ ዘመን ያላት ቢሆንም የሰው ልጅ ግን ባለ መግባባት እየተግባባ ዘመኑን እያሳለፈ አብሮ መኖሩን ቀጥሎል፣
በዚች አጭር ፁሁፌ ውስጥ ለማስገንዘብ ወይም ለማሳሰብ የምፈልገው ኣንደሚከተለው ይሆናል።
መፍትሔ ያጣ ትውለድ ስል መፍትሔን በጋራ ለማምጣት ጭምር በእሳቤነት እንዲያዝልኝ ስል አስገነዝባለው።
እንደሚታውቀው የ ኢትዮፕያ ፖለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ መጉአዝ ከጀመረ ዘመን አስቆጥሮል ምንም እንኩአን ዲሞክራሲ የሚለው ቃል ከህዝብ ውስጥ ላም አለኝ በሰማይ ሆኖ ይኸው እስከዛሬ ድረስ ዜጎች ማንነታቸው ተዋርዶና ተንቆ ከሃገር ኣልፎ ተርፎ በስደት ኣለም ወስጥ ህይውታቸው በከንቱ እያለፈና የህይወት መራራ ጽዋን እየተጎነጬና አሳር መከራቸውን እየበሉ መኖር ከጀመሩ ዘመናት ተቆጥረዋል።
ጎበዝ አንድ ቦታ ላይ ቆም ብለን እንደ ትውልድ እንደ ዜጋ እንደ ኢትዮፕያዊነታችን ማሰበና መወሰን እንዳለብን ለሁሉም ኢትዮፕያዊ መፍትሔ ሊያስገኝ የሚችል መስመር ላይ መሆን እንዳለብን በጥብቅ ላስገነዝብ እወዳለው።
ችግሮቻችን ምንድናቸው_መፍትሔውስ ምንድነው
ውድ አንባብያን በቅድሚያ እራሳችንን መፈተሽ ስላለብን ወዳሳለፍነው ሶስት መንግስታቶችን ማየት ያለብን ይመስለኛል በንጉሱ ጊዜ ምንም አንድነታችንና ውበታችን ክብሩን ተብቆ ቢኖርም በከበርቴውና በጭሰኞው መካከል ሰፊ የጭቆና አገዛዝ መኖሩና እየተባባሰ መምጣቱ፧
በመሬት ላራሹና በከበርቴ መሃል ከፍተኛ ልዩነት መከሰቱ ህዝቡ ለአመፅና ለለውጥ እንዲነሳ አድርጎታል።
ውድ ኣንባብያን በተቀሩት ሁለት መንገስታቶች ማለትም በደርግና በኢህአዲግ ወይም ራሱን ቲ ፒ ኤል ኤፍብሎ በሚጠራው አገዛዝ ላይ የነበሩትና እስካሁንም ያለው የዲክታተር አገዛዝን ለጊዜው ወደ ጎን አድርጌው ትኩረቴን በሶስቱ መንግስታት ዘመን የነበርውን የአምስት አመት መዋቅር መርሃ ግብር የዕቅድና አፈፃፀም ላይ ማተኮርና የመልካም ኣስተዳደር ጉድፈቶች ለመዳሰስ እሞክራልው።
በመጀመሪያ ሶስቱም መንገስታቶች ያቅዱት የነበረው የአምስት አመት መርሃ ግብር ዕቅዶች ተመሳሳዮች ሲሆኑ በአፈፃፀም ዙሪያ ላይ ከፍተኛ ችግር ያልባችው በቢሮክራሲ መረብ የተጠመዱና ለአንድ ፓርቲ አገዛዝ እንደ ፖለቲካ መሳሪያ የሚያገለገሉ ከመሆናቸው በስተቀር ለህዝቡ ያመጡት ወይም የለወጡት የኑሮ እድገት ደረጃ አለመኖሩ በግልጽ የታወቀ ነው
ለምሳሌ በዘመነ ሃይለስላሴ ጊዜ ያልተማረ ይማር ሲባል በደርግ ጊዜ ማይምነት ይጥፋ፧ይባል ነበር ባሁኑ መንግስት ደግሞ ትምህርት እስከ ገጠር እናዳርሳለን፧ እስከማለትና እንደ ዕቅድ አውጥቶ ከማየት በስተቀር ወይንም ሰማንያ ኣምስት በመቶ በግብርና ሙያ ላይ ላለው ህዝባችን ያመጣው ምንም ኣይነት መሰረታዊ ለውጥ እንደሌለ ታሪክ ይመሰክራል። ይህ ብቻ አይደለም በሶስቱም መንገስታት ያለ የዲሞክራሲ መንፈስና መብት ፧የነፃው ፕሬስ እምድምታ፧የሰብአዊ መብት አያያዞች፧የግለሰብና የቡድን መብቶች ከዕለት ወደ ዕለት ከዘመን ወደ ዘመን ከመንግስት ወደ መንግስት እየተባባሱ መምታጣቸው ልንክደው የማንችለዉ የታሪክ ሃቅ ነው።
ይህም በመሆኑ የተነሳ ዛሬ ማንነታችን በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር አስከፊ ከመሆኑም የተነሳ አንገት ደፍተን እንድንሔድ አድርጎናል።
ውድ ኣንባብያን ስላለንበት ሁኔታ በዙ መዘርዘር ይቻል ነበር ግን ከህዝብ የተደበቀ አንዳችም ነገር ስለማይኖርና ሊኖርም ስለማይችል ውስጡን በዝርዝር ጉዳይ ከመተንተን ይልቅና መፍትሔ ያጣ ትውልድ እየተባልን ዘመን ከማስቆጠር ይልቅ እንደ አትይፕያዊ ወይም እንደ ዜጋ ቆም ብለን ማሰብና መወሰን ያለብን ጉዳይ መሆኑን በጥብቅ መገንዘብ አለብን።
ይህ እንዳለ ሆኖ በዋነኛነት ሊያሳስበንና ትኩረት ልንሰጠው የሚገባው ወደ መፍትሔው ኣቅጣጫ ማምራት ያለብን በምን አይነት መልኩ ነው የሚለውን ትልቅ ጥያቄ በአንክሮ ማየትና ጠለቅ ባለ ሁኔታ መመልከት ያለብን መሆኑን ማስገንዘብ እወዳለው።
በመጀመሪያ የሰው ልጆች በዚህ አለም የመኖር መብት ከእግዚያብሔር የተሰጠ ፀጋ መሆኑን እራሳችን ለእራሳችን ልናረጋግጥ ይገባናል ማንም ነፃነትህን ሊሰጥህም ሆነ ሊቀማህም ኣይችልም።
የሰው ልጅ ነፃነቱን ለማግኘት የግድ በብሔር መደራጀት የለበትም በተለይም አትይፕያን የሚያህል ታላቅ ማህረበረሰብ ወይንም \ ግሬት ሲቪላይዜሽን\\ባለበት ሃገር ላይ የብሔር የትግል አቅጣጫ የነፃነትን ጉዞ ከማስረዘም ውጪ መሰረታዊና ቅጽበታዊ ለውጥ ያመጣል በሎ ማሰቡ የማይታመን ከመሆኑም አልፎ በአይናችን እያየነው ያሉትን ችግሮች ከመፍጠሩም የተነሳ ከባድ እንቅፋት ሆኑኣል።
በአፍሪካ በዲሞክራሲ በለፅገዋል የትባሉትን ሁለት ሃገሮች ጋናና፧ኬንያ በምሳሌነት መውሰድ ይቻላል።
እነዚህ ሃገሮች በህገ መንገስታቸው ወስጥ በዘርና በሃይማኖት መደራጀት በህግ የተከለከለ በመሆኑ ዛሬ ላሉበት የዲሞክራሲ ዕድገትና የፖሊሲ ለውጥ እድገት ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተላቸው የማይካድ ሃቅ ነው።
በብሔር መደራጀት የገዚውን ፓርቲ ሲልጣን ከማራዘምና የመከራን ጉዞ ከማብዛት ውጪ ምንም ኣይነት ለውጥ እንደማናመጣበት እኛው እራሳችን ምስክር ለመሆን የቻልንበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።በብሔር መደራጀት ወይም\ ኢትኖ ፌዴራሊዝምን\ በስርአት ውስጥ እንደ ኣገዛዝ ስልት ቆጥሮ ኣንድን ትልቅ ህብረተሰብን በጎሳ ከፋፈሎ ስልጣንን ያለ ገደብ ለመቆናጠጥ ሲባል ብቻ መዋቅርን ዘርግቶ የወደፊትን መረሃ ግብር ዕቅድ መተለሙ ከህዝብ ጥላቻ ማትረፍ እንጂ ሌላ ገጽታ እንደሌለው በስልጣን ላይ ካለው ገዢው መንግስት ትልቅ ትምህርት መውሰድ እንችላለን።
በመሆኑም ዛሬን ላይ ቆም ብለን ማሰብና የወደፊት የነፃነትን ጉዞ ወይንም የትግል ኣቅጣጫ ዛሬን ላይ ሆነን መወሰን ይኖርብናል።
ባሁኑ ሰኣት የህዝባችን ነፍስ ወከፍ ገቢ በቀን ከኣንድ ዶላር በታች ሲሆን ገዚው መንግስት ትውልድ ሊከፍለው የማይችለው የብድር ዕዳ አስራ ስምንት ነጥብ ዜሮ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ከአለም ባንክ የተበደረ መሆኑን ይፋዊ ምንጮች ኣረጋግጠዋል።
አለመታደል ሆኖ ወይንም የራሳቸውን የፖለቲካና ኢኮኖሚ ፍላጎት በቻ ለማሞላት ዛሬ ሃያላን ሃገሮችና ኣለም ባንክን ጨምሮ የገዢው መንግስትን ዲሞችራሲያዊ ጥሰትና ኢሰባዊ ድርጊቶችን ግምት ውስት ባለማስገባት ትውልድ ላይ ዕዳን ለመከመር ወይንም \ሞደርን ኮሎናይዜሽን\ለሃገራችን የገንዘብ ብድር በገፍ እየተሰጠ ያለበት ሁናቴ ላይ ደርሰናል።
ሲለዚህ መፍተሔ ይሆናል ብዬ ለማንሳት የሚሻው ትልቁ ነገር ቢኖር መሰርታዊ ለውጥ\ቤዚካል ቼንጅ\ያስፈልገናል ይህም ሲባል ህብረተሰባችን ለለውጥ ባንድነት ታጥቆ መነሳት ኣለበት ባይ ነኝ ማለትም መሰርታዊ ለውጥ ሲባል በኣስተሳሰብ፧በኣንድነት አደረጃጀት፧ `፧ከብሔር ኣስተሳሰብ መውጣት፧ ራስን ወይም ድርጅቶችን ለዕርቅና ለውህደት ማዘጋጀት፧ሃገራዊ ፍላጎቶች\ጠቀሜታዎችን ከግል ጥቅሞች\ፍላጎቶች\አጥብቆ መለየትና፧ ወዘተ ናቸው።
በርግጥ ባሁኑ ሰኣት በሰላማዊ ትግል ለውጥን ማስብ በጋን ውስጥ እንዳለ መብራት እየሆነብን መምጣቱ የሁለት ኣስር ኣመታቶች የምርጫ ዘመን ልምዶቻችን እንደሆኑ ኣብዛኛው ህዝባችን የሚስማማበት ይመስለኛል ሆኖም ግን ባለው ቀዳዳ ተጠቅመን ኣሁንም በሰላማዊ ትግል መሰረታዊ ለውጥ እናመጣለን የሚሉም ሃይሎች በመኖራቸው እሰየው በርቱ ከማለት ውጪ ምንም ኣይነት ሃሳብ መሰንዘር ኣልፈልግም።
ከየትም ኣምጪው ዱቄቱን ፍጪው ይባል የለም እንደሚታወቀው ሁሉ ዲያስፖራው ከሰላማዊ ሰልፍ ጀምሮ ለለውጥ ያስፈልጋሉ የሚላቸውን ሃይሎች በሙሉ እየተጠቀሙ መሆኑ በግልፅ ይታወቃል ይሁንና የህዝባችን ስቃይ ከቀን ወደ ቀን ከዕለት ወደ እለት እየጨመረ መጥቶል ስለዚህ ህዝባችንን ከዚህ ኣስከፊ ጥቃት ለመታደግና ለማዳን ታጥቀን ባንድ ኣላማ መነሳትና ለለውጥ መዘጋጀት እንዳለብን ለማስገንዘብ እወዳለው።ይህም የሚሆነው ከብሔር ደረጅት ኣስተሳሰብ ነጻ ስንሆን ነው።
ተፃፈ
በዳንኤል ኣላዩ ዘለቀ
No comments:
Post a Comment