በዳንኤል አላዩ ዘለቀ
october 22 2014
ውድቀት ወይንስ እድገት፣
እንደሚታወቀው ሃገራችን ኢትዮፕያ በተፈጥሮ ለምለምና የከርሰ ምድር ሃብቱኣ በጥበብ ታግሶ የህዝቦቻን ዘለቄታዊ ፍላጎቶች ማሙላት የምትችል ሃገር ሆና ሳለ በተለያየ ጊዜ የሚፈጠሩባት ገዚዎች ለቡድን ኣልያም ለጎሳና ለፓርቲ ጥቅም ከማስከበር ውጪ ከህዝብ የተወከለና ለህዝብ የቆመ ፓርቲም ሆነ መንግስት አለመፈጠሩ ይሔው ዛሬም ህዝባችን ከጨለማ ወደ ጨለማ ከድህነት ወደ ድህነት እየተሽጋገረ መምጣቱ ኣሳዛኝ አድርጎታል።
ለመሆኑ ዳቦና ዲሞክራሲ በጠፋበት ሃገር ላይ ሊታለም የሚችለው ውድቀት ወይንስ እድገት መልሱን ለኣንባብያን ትቻቼዋልው።
በመሰረቱ ባሁኑ ዘመን የህብረተሰባችን ንቃተ ህሊና ከሚገባው በላይ አድጎል ባይባልም መብቱን ለይቶ ማወቁና ለመብቱ ተቆርቖሪ እየሆነ መምጣቱ ከዘመን ዘመን ብረት አንጋች ለሆኑት ገዢዎቻችን የእግር እሳት ከመሆኑም አልፎ ዲሞክራሲያዊ መብቱን ገዢዎች እንዳሻቸው ሊነፍጉትም ሆነ ሊሰጡትም እንደማይችሉ በሚገባ እያስመሰከረ ነው።
ዛሬ በሃገራችን ህብረተሰቡ ምሳ በልቶ እራት የማይደገምበት ሁኔታ ላይ ደረሰናል የዕለት ተዕለት የኑሮ ግዥፈትና ውጣ ውረድ ያሳሰበውና የዕለት ጉርሱን ለመቅመስ የሚታገልን ህዝብ እድገት ተፈጥሮልሃል፣ኑሮህ ተሻሸሎል ብንለው እራስን ከማታለል ውጪና የለውጥን ዕድሜ ከማቅረብ ውጪ የሚፈጠር ነገር ኣለመኖሩ ግልጽ ነው።
በመሰረቱ በማደግ ላይ ያሉ ሃገሮች የእድገት መጠናቸው በፐርሰንት ሲለካ ከኣንድ እስከ ሶስት ፐርሶንት ሲሆን አሜሪካ፣ ቻይናና ህንድ የእድገት መጠናቸውን በተጨባጭ ማስረጃ እይታ ማሳያ ላይ በማሳየት ይገኛሉ።
ለመሆኑ የኢትዮፕያ እድገት ኣስራ ሃንድ ፐርሶንት ኣድጉኣል እየተባለ ዲስኩር ሲነገርና መለከት ሲነፋ መስማቱ በተለይም ለነቃና ለባነነ ህብረተሰብ ይህን ማሰማቱ ኣሳዝኝ ከመሆኑም የተነሳ ኣውቆ ለመታለል እንኮን እጅግ በጣም የሚከብድና የሚዘገንን ነገር ነው። በመሆኑም የምግብ ዋስትና ወይም \ፉድ ሰኩሪትይ\ በሃገራችን ኣስተማማኝ ካለመሆኑ የተነሳ ኣሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ግልጽ ነው ዛሬ በሃገራችን ጥቂቶች በልጽገውና ከብረው ብዙሃኑ የደኸየባት ሃገር ስትሆን ፣በቀን ሶስት ጊዜ የሰው ልጅ መመገብ ያልቻለበት፣በሃያ ኣንደኛው ክፍለ ዘመን ከሳይበር ቴክኖሎጂ የተራራቀ ህብረተሰብ የሚገኝባት ሃገር፣የዲሞክራሲው ምህዳር የታፈነበት ሃገር፣የህብረተሰቡ የነፍስ ወከብ የቀን ገቢ ከኣንድ ዶላር በታች የሆነባት ሃገር፣የኢኮኖሚ ውድቀትና የምንዛሪ ግዥፈት የሚከሰትባት ሃገር፣ላይ እድገት ወይስ ውድቀት፧ መልሱን ለኣንባብያን ትቼያለው። የትራንስፎርሜሽን ዕድገት እየተባለ ባለው ኣንድ ሚዲያ የሚደሶከረው ከህዝባችን ዕድገት ቁጥር ጋር ሲነጻጸር በግልጽ የሚታውቅ ከመሆኑም የተነሳ ዕድገት ተብሎ በባዶ ሜዳ ላይ ዲስኩር መደስኮሩ የውድቀት ባቡር ላይ ከመሳፈር ውጪና ወደማይፈታ የጎሳ ግጭት ማምራቱ ኣይቀሬ ነው።
ለኣንድ ሃገር ዕድገትም ሆነ ለህዝቦች ኑሮ መሻሻልና ኢኮኖሚን ማሳደግ የሚቻለው በተቀዳሚነት የህዝቦችን ዕኩልነት ፣ኣንድነት፣ዲሞክራሲያዊ መብት፣ነጻነትንና ሰብኣዊ መብቶች ሲጠበቁ በቻ መሆኑኖ በኢኮንሚና በፖሊቲካው ከበለጸጉት ሃገሮች ትልቅ ትምህርት መውሰድ ይቻላል ህዝብን ማፈንና የመጻፍ፣የመናገር ፣የመደራጀት መብቶችን መከልከልና መሰረት ኣልባ የሆነውን የትራንስፎርሜሽን ዕድገት እያሉ በህዝብ ላይ መጫወት ወደማያባራ የርስ በርስ ግጭት ውስጥ እንደሚገባ ልናውቅ ይገባል።
ሰሞኑን እጅግ በጣም የገረመኝ ጠቅላይ ሚኒስተሩ በፓርላማው ላይ ብሎገሮች ላይ ክስ መስርተናል ኣሁንም በሚገባ እንከሳለን ዘብጥያም እናወርዳለን ሲሉ ሰማሁና ንግግራቸው ኣሳፈረኝም ኣሳዘነኝም ገዢው መንግስት ኣሁንም ዕድገት የሚልው ስርዎ ቃሉ የገባቸው ኣልመስልህ እያለኝ ነው ምክንያቱም የትኛውም ሃገር በኣለም ላይ ያለ ዲሞክራሲን መሰረት በማድረግ ነው ኢኮኖሚውን ያበለጸጉት ለምሳሌ የኢትዮፕያ ህዝብ የተትረፈረፈ የኑሮ ደረጃ ላይ ቢሆን እንኾን ሃገርና የህዝብ ኑሮ ስላደገ ብቻ ለዘመናት ስልጣን ላይ እቆያለው ብሎ ማሰቡና የረጅም ኣመት ዕቅድ ማቀዱ የማይቻል መሆኑን ማንም ሊገነዘብ ይገባዋል።
በመሰረቱ ዕድገት ተብሎ ሲታሰብ ከተለያየ ኣንግሎች ሊታዩ የሚገባቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ ሊታወቅ ይገባል በህዝቦች ፍቅርና በነጻ ኣስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ያለገደብ ማስከበርና ሃገር ወዳድ ዜጋን ማፍራቱ ለኣንድ ሃገር ዕድገትና መሰረታዊ ቁልፍ ሚና የሚጫወት መሆኑን በተሞክሮም ሆነ በስኬታማነቱ ከሌሎች ሃገሮች መማሩ ጥሩ ነው።
ባሁኑ ሰኣት ህዝባችን መሰረታዊ ፍላጎቶች የሚባሉትን ወይንም \ቤዚክ ነሰሲቲ\ምግብ፣መጠለያ፣ውሃ ወዘተ የመሳሰሉት ባልተሞሉበት የህይወት ውጣ ውረድ ላይ እንደሚገኝና ዕውነታው ይሄ ሆኖ ሳለ በግድ ለማሳመን የሚነፋው ፕሮፖጋንዳ ግን የችግሮችን ቀውስ እያባባሰ ከመምጣት በስተቀር ምንም ኣይነት መፍትሔ እንደማያመጣ ሊጤን የሚገባው ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ሊሰመርበት ይገባል።
እውነታውም ይሔ ሆኖ ሳለ የዲሞክራሲን ጉድፈቶች በልማትና በብልጽግና ስም የፖለቲቻ ኣጀንዳን መዶስኮሩ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ሊባል ስለሚችልና ወደ ፖለቲካን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ ሲለሚያስገባ ሊታሰብበት የሚገባው ትልቅ ጉዳይ መሆኑን በጹሁፌ ለማስገንዘብ እወዳለው።
ተጻፈ
በዳንኤል ኣላዩ ዘለቀ
posted By Daneil Aleyu zeleke
No comments:
Post a Comment