(ኢ.ኤም.ኤፍ) አረና በትግራይ የሚንቀሳቀስ ተቃዋሚ ፓርቲ ነው። ይህ ፓርቲ በመጪው ምርጫ ህወሃትን ከሚያሰጉት ፓርቲዎች አንደኛው መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የፓርቲውን ዋና አስተባባሪዎች ማሰር የህወሃት አንደኛው ስራ ሆኗል። በቅርቡ እነ አብርሃም ደስታን ለእስር የዳረገው የህወሃት አስተዳደር በትግራይ ሌሎች የአረና ደጋፊዎች የሚላቸውን ግለሰቦች ማዳበሪያ እና ልዩ ልዩ እርዳታዎች እንዳያገኙ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ በመጪው ምርጫ ያሰጉኛል ብሎ የሚያስባቸውን ሰዎች ያለምንም ምክንያት ከቤታቸው ወስዶ በማሰር ላይ ነው። አምዶም ገብረስላሴ ከትግራይ እንደዘገበው ከሆነ፤ ሰሞኑን ደግሞ ሁለት የአረና ከፍተኛ አመራሮች ታስረዋል። ሙሉ ዘገባው ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል።
========================
በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሑመራ ወረዳ ዳንሻ ከተማ ኣቶ ዘነበ ሲሳይ የዓረና ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባል ዛሬ ማከሰኞ 25 / 02 / 2007 ዓ/ም ከቀኑ 7 ሰዓት ፖሊሶቸ ፖሊሰ ጣበያ ትፈለጋለህ በለው ከመኖርያ ቤቱ ዳንሻ ከተማ ወሰደው ኣሰረውታል።
========================
በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ቃፍታ ሑመራ ወረዳ ዳንሻ ከተማ ኣቶ ዘነበ ሲሳይ የዓረና ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባል ዛሬ ማከሰኞ 25 / 02 / 2007 ዓ/ም ከቀኑ 7 ሰዓት ፖሊሶቸ ፖሊሰ ጣበያ ትፈለጋለህ በለው ከመኖርያ ቤቱ ዳንሻ ከተማ ወሰደው ኣሰረውታል።
በሌላ ዜና ኣቶ ኣማረ ተወልደ የዓረና ቁጥጥር ኮሚቴ በሑመራ ከተማ ዛሬ ማከሰኖ 25 / 02 / 2007 ዓ/ም ከቀኑ 10 ሰዓት በፖሊሰ ታስረዋል። ኣቶ ኣማረ ተወልደ ከሳምንት በፊትም ታሰረው በ3000ብር ዋሰ ተለቀው ነበር።
ከትናንት በስተያም በማይካድራ ከተማ የዓረና ስራ ኣስፈፃሚ ኣባሉ ኣቶ መሰለ ገብረ ሚካኤል ታስረው እንደነበሩ የሚታወስ ነው።
የህወሓት መንግስት የዓረና ኣባላተ በየቀኑ ማሰር፣ ማነገላታትና መደንደብ እቅድ ኣወጥቶ የጥላቶች ክትትል ቡድን በማደራጀት እየፈፀመው ይገኛል።
ኣብራሃ ደስታ፣ ኣያሌው በየነ፣ ኣድሃና ንጉሰ፣ ገብረዋህድ ሮምሃ በጠላትነት ፈርጆ በእስር እያማቀቃቸው ይገኛል። ኣብራሃ ደስታ ነገ እሮብ 26 /02 / 2007 ዓ/ም በልደታ ፍርድ ቤት ይቀርባል።የሸገር ኑዋሪዎቸ በልደታ ፍርድ ቤት ተገኝታቹ እንደተለመደው ደጋፋቹ እንድትለግሱላቸው እንላለን።
በነገራችን ላይ እነ ኣብራሃ ደስታ ከማእከላዊ እስር ቤት ወደ ቂሊንጦ ተዘዋውረዋል። ማንኛውም ዜጋ እነ ኣብራሃ ደስታ ቂሊንጦ በመሄድ መጠየቅ ይችላል።
posted By Daneil Aleyu Zeleke
No comments:
Post a Comment