Saturday, 29 November 2014

የዞን ዘጠኝ ትግባኝ ውድቅ ሆነ!

በሽብር “ ተግባር ተጠርጥረው በማረሚያ ቤት ከሚገኘት 9 የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች መካከል ስምንቱ ተከሳሾች የዋስትና መብታቸው አንዲከበር ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገቡት ይግባኝ ውድቅ ተደረገ፡፡
ስድስቱ የዞን9 ጦማርያን እና ሁለቱ ወንዶች ጋዜጠኞች ጉዳያቸው በቋሚነት በሚታይበት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ መብታቸው አንዲከበርላቸው ጠይቀው ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቅርበው ነበር፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጉዳዮን ከጠበቆች እና ከአቃቤ ህግ በመስማት ውሳኔ ለመስጠት አንድ ተጨማሪ ቀጠሮ የወሰደ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ በሰጠው ውሳኔ ያለምንም ማብራሪያ በጸረ ሽብር ህጉ በመከሰሳቸው ዋስትና አይገባቸውም በሚል ምክንያት የስምንቱን ይግባኝ ባዮች አቤቱታ ውቅድ አድርጎታል፡፡
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ተያይዞ ይገኛል፡፡
tekelay frd bet
Share Button


No comments:

Post a Comment