ዛሬ በዋለውም ችሎት የመከላከያ ምስክርነታቸውን የሰጡት የቲሞች አባት የሆኑትና በነኡስታዝ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ 12ተኛ ተከሳሽ የሆኑት ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ መሆናቸው ተገልፆዓል።
የቲሞች አባት የሆኑት ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ የመከላከያ ምስክርነታቸውን የሰጡት በነአቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ በ1996 የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)(ለ)፣ 38(1) እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጠር 652/2001 አንቀፅ 3(1)(4)(6) እና 4 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ከ2001 ጀምሮ በህቡዕ በተደራጀው ቡድን አባል በመሆን ይህንን የቡድኑን ዓላማ ለማስፈፀም የሚያስችለውን ስልጠና ውጪ ሀገር በመሄድ ስልጠና በመውሰድ ከተመለሰ በኋላ፤ ይህንኑ ስልጠና ለቡድኑ አባላት በመስጠት ለዓላማው አፈፃፀም ስትራቴጂ በማውጣት ሲንቀሳቀስ ከቆየ በኋላ “የሙስሊሙ ኅብረተሰብ መፍትሄ አፈላላጊ” በማለት ራሱን የሰየመው ኮሚቴ ፀሐፊ በመሆን በተለያዩ የሰደቃ ፕሮግራሞች ላይ በመሳተፍና በመንቀሳቀስ ሲል በሃሰት ለተወነጀሉት ለ9ኛ ተከሳሽ ለሆኑት ለኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ ሲሆን በተለይም በጭብጡ ላይ ማዕከላዊ (ወንጀልና ምርመራ) እስር ቤት ውስጥ የደረሰባቸውን የመብት ጥሰት እና ኢ-ሰብዓዊ የሆነ ሰቆቃቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።
ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ አብረው በማዕከላዊ እስር ቤት እንደነበሩና ለ102 ተከታታይ ቀናት ከፍተኛ ቅዝቃዜና ብርሃን የሌለበት በተለምዶ ሳይቤሪያ ተብሎ በሚጠራው እስር ቤት እንደተሰሩ ገልፀው፥ ቃላቸውን የሰጡት ከቤተሰብና ከጠበቃ ከመገናኝታቸው በፊት መሆኑን፣ ከፍተኛ ድብደባና እንግልት ከመፈፀሙ የተነሳ እግሮቹ ላይ ጠባሳና ቁስል እንዳለ፣ ብልቱን አሰቃቂና ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መልኩ እንደደበደቡት አስረድቷል። በዛሬው ችሎት ላይ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ በኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ ላይ በማዕከላዊ እስር ቤት የድረሰበት ስቃይና መከራ ሲገልፅ የፍርድ ሂደቱን ሲከታተሉ የነበሩ ታዳሚያን በከፍተኛ ቁጭትና በሃዘን ድባብ ውስጥ ተውጠው እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል።
የመከላከያ ምስክርነታቸውንም ከሰጡ በሁዋላ በፌደራሉ አቃቤ ህግ የቀረበላቸውን መስቀለኛ ጥያቄዎች በአስደናቂ ሁኔታ መልሰ ሰጥተው ችሎቱ ተጠናቋል።
የፍርድ ሂደቱ ነገም ይቀጥላል።
©የቂሊንጦ ልሳን
posted By Daneil zeleke
No comments:
Post a Comment