ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቱን ተጠቅሞ የፍትህ ጋዜጣና መጽሄትን ሲያዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ካንጋሮው ፍርድ ቤት 3 ዓመት የእስር ቅጣት ማስተላለፉ ተመለከተ::
የፍርድ ትዕዛዝ እስኪተላለፍበት ለ2 ሳምንታት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የቆየው ጋዜጠኛው በ እዚያው እስር ቤት ውስጥ አንገቱ ላይ የሚያስራትን እስካርቭ እንዲያወልቅ በፖሊሶች ት እዛዝ ቢሰጠውም ጋዜጠኛው አላወልቅም በማለቱ ሰው እንዳይጠይቀውና ብቻውን እንዲታሰር መደረጉን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል::
ጥቅምት ፲፮(አስራ ሥድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-
የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት፣ ግዙፍ ባልሆነ ማሰናዳትና የመንግስትን ስም በማጥፋት ወንጀል ተከሶ ሲከራከር ከቆየ በሁዋላ፣ የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 9ኛ ወንጀል ችሎት በ3 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል። ጋዜጣውን ሲያሳትም የነበረው ማስተዋል የህትመትና ማስታወቂያ ስራ ድርጅት ደግሞ በ10 ሺ ብር እንዲቀጣ ሲል ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል። ተመስገንም ሆነ ጠበቃው የእስር ማቅለያ ሳያቀርቡ ቀርተዋል።
ኢሳት ምርጫው እስኪጠናቀቅ ጋዜጠኛ ተመስገን እንዲታሰር መወሰኑን የደህንነት ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ መዘገቡ ይታወሳል። የጋዜጠኛ ተመስገን መታሰር በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ታሰሩ ጋዜጠኞች ቁጥር 18 አድርሶታል።
በቅርቡ ከ18 ያላነሱ ጋዜጠኞች በተመሳሳይ ወንጀል እንደሚከሰሱ መረጃ ከደረሳቸው በሁዋላ ከአገር እንደወጡ ይታወቃል።ችሎቱን ከውጭ ሆነው ይከታተሉ የነበሩ ለተመስገን አድናቆታቸውን በጭብጨባ ሲገልጹለት እንደነበር የአይን እማኞች ገልጸዋል
posted By Daneil Zeleke
No comments:
Post a Comment